ሳም ሊካራዶ ለአሜሪካ የሕግ አውጭው ም/ቤት (ዩኤስ ኮንግረስ) አባል ለመሆን እየተፎካከሩ ነው

ሳም ሊካራዶ ለአሜሪካ የሕግ አውጭው ም/ቤት (ዩኤስ ኮንግረስ) አባል ለመሆን እየተፎካከሩ ነው። የለውጥ ትኩረታቸውን ያደረጉት ደግሞ በሚከተሉት ጉዳዮች ላይ ነው፦
– የዜጎች ቤት አልባነት ማስወገድ
– ወንጀሎችን በከፍተኛ ደረጃ እንዲቀንሱ ማድረግ
– የኑሮ ውድነትን መቀነስ እና
– ልዩ ልዩ ህጎች እንዲረቁ፣ ብሎም ተግባራዊ እንዲሆኑ መንቀሳቀስ

Sign up for campaign updates

የአሜሪካ ኮንግረስ ባለፉት በርካታ ዓመታት ስኬትና ውጤት አላስመዘገበም፣ የኮንግረስ እጩ ተወዳዳሪው ሳም ሊካርዶ፣ ይህን ደካማ ጎን መለወጥ አለብን ፣ “ማድረግም ይቻላል” ይላሉ!! ለዚህም የዜጎችን መሰረታዊ ችግሮችን ማስወገድ ዋነኛ ተግባር እንደሆነ ያምናሉ፡፡ በተለይም ለሚወክሉት የወረዳ 16 (ድስትሪክት 16) ከደቡብ ምዕራብ የሳን ፍራንሲስኮ የባህር ሰላጤ አካባቢ በሳንታ ክሩዝ፣ እስከ ፓሲፊክ የባህር ዳርቻ ድረስ ያለውን፣ የሳንታ ክላራ እና የሳን ማቲዮ ግዛቶች ነዋሪ ለሆኑ ዜጎች ያለባቸውን ዘርፈ ብዙ ችግሮችን ለማስወገድ በቁርጠኝነት ተነስተዋል።
ተጨባጭ ለውጥ ከፈለጉ ድምፆን ለእጩ ተወዳዳሪው ለሳም ሊካርዶ ይስጡ!!
የኮንግረስ እጩ ተወዳዳሪው ሳም ሌካርዶ የለውጥ አጀንዳዎች በስድስት ዋና ዋና ጉዳዮች ላይ ያተኩራሉ

ጎዳና ተዳዳሪነትን ማስወገድ

የቤት አልባ እና የጎዳና ተዳዳሪነት ዋነኛ መንስኤ፣ የዜጎች የመግዛት አቅምን የሚመጥኑ/አፎርደብል መኖሪያ ቤቶች አለመኖራቸው ነው። የሳን ሆሴ ከንቲባ ሆነው ባገለገሉበት ዘመን ተግባራዊ እና ውጤታማ መፍትሄዎች በማመንጨት ለከተማዋ ነዋሪዎች በዝቅተኛ ዋጋ ቤቶች ለመግዛት እንዲቻል አድርገዋል። አሁንም በፌደራልና በአካባቢ ከሚመለከታቸው አካላት ተመሳሳይ መፍትሔዎችን ተግባራዊ በማድረግ ቤት አልባነትን ችግር ማስወገድ ከቀዳሚ ትኩረቶቻቸው መካከል ነው፡፡

የቤት አቅርቦት

የቤቶች ዋጋ በጣም ከፍተኛ መሆኑ ለብዙዎች ትልቁ ፈተና ነው። ይህ ደግሞ ቤተሰቦችን፣ እንዲሁም በሺ የሚቆጠሩ ሰራተኞችን ለከፍተኛ ችግር ሲያጋልጥ ይታያል። በመሆኑም የአሜሪካ ኮንግሬስ ለዚህ ችግር ልዩ ትኩረት እንዲሰጥ ይደረጋል።
ለምሳሌ ሰዎች የማይኖሩባቸውን ባዶ ህንፃዎች ለዋጋ ተመጣጣኝ ወደሆኑ የጋራ መኖሪያ (ብዙ ቤተሰብን ወደሚይዙ ቤቶች) መለወጥ፣ እንዲሁም ሌሎች ማበረታቻዎችና ውጤታማ መፍትሄዎች በመጠቀም ችግሩን ማስወገድ።

የኑሮ ውድነት

የኑሮ ውድነት ለአሜሪካ ቤተስቦች በጣም አስቸጋሪ መሆኑ ይታወቃል። በተለይ ከዋጋ ንረት/እንፊሌሽን ጋር፣ ከመሰረታዊ የምግብና የፍጆታ እቃዎች፣ የጤና ጥበቃ፣ እንዲሁም የህጻናት እንክብካቤ ጋር በተያያዙ የታክስ እና የዋጋ ድጎማ ድጋፎች በማድረግ ይህን ትልቅ ችግር በከፍተኛ ደረጃ መቀነስ።

ወንጀልና የጦር መሳሪያ ቁጥጥር

ሳም ኪካርዶ የሳን ጆሴ ከንቲባ በነበሩበት ግዜ ያመጡት ስኬት፣ የፓሊስ፣ የማህበረስብ አገልግሎት መኮንኖች፣ እንዲሁም አትራፊ ያልሆኑ ድርጅቶች ጥምረት በመመስረት ወንጀሎችን ለመቀነሰ ጥብቅ የጦር መሳሪያ ላይ ቁጥጥሩ ጥብቅ ማድረግ አንዱ ነበር፡፡ በአሜሪካ ኮንግሬስ ይህ የስኬት ሞዴል ተግባራዊ እንዲሆን ፣ እንዲስፋፋ ለማድረግ ይሰራሉ።

የአየር ንበረት ለውጥና የአካባቢ ጥበቃ

የአየር ንበረት ለውጥና የአካባቢ ጥበቃ
በሳን ጆሴ ከንቲባ በነበሩበት ወቅት የከተማው የጋዝ ልቀት/ግሪን ሀውስ ጋዝ ኢሚሽንስ በ 36% እንዲቀንስ በቁርጠኝነት ሰርተዋል፣ የንጹህ ሃይል/ክሊን ኤንርጂ እቅርቦት እንዲጨምር፣ በርካታ ቦታዎች ለግንባታ እንዳይውሉና አረንጓዴ የህዝብ ቦታዎች መሆናቸው እንዲቀጥል፣ የዘላቂ የትራንስፓርት ግንባታ እንዲዘረጋ በትጋት ሰርተዋል። ተመሳሳይ ህጎችና ፓሊስዎች በአሜሪካ ኮንግሬስ ለመግፋት በቁርጠኝነት ይንቀሳቀሳሉ።
6ኛ) የሴቶች የመምረጥ እና የወሊድ መብቶች
መሰረታዊ የምንላቸው መብቶች ላይ ጥቃት ሲሰዘር አሻፈረኝ ማለትና በቁርጠኝነት መታገል አለብን፡፡ ሳም ሊካርዶ ኮንግረስን ሲቀላቀሉ እነዚህ በቅርብ ዓመታት ከፍተኛ ጥቃት ሲሰነዘርባቸው የቆዩ መብቶችን ለመከላከል አጥብቀው ይሰራሉ፡፡ የሮ ቨ ዋዴ መቀለበስ አንዱ ማሳያ ነው። የሴቶች የወሊድ መብቶች፣ ከምርጫና ጋር የተያያዙ መብቶች፣ የዜጎችን ድምጽ የመስጠት መብቶች ለመገድብ የሚደረጉ አግላይና ዘረኛ አካሄዶችን አጥብቆ መዋጋት አስፈላጊ ነው፡፡ እጩ ኮንግሬስማን ሳም ሌካርዶ ይህን ወሳኝ ጉዳይ ተግባራዊ ለማድረግ በቁርጠኝነት ተነስተዋል።

ከላይ የተዘረዘሩት ዋና ዋና ጉዳዮች ለእያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ አሜሪካዊ ህይወት ፋይዳ ያላቸው ናቸው!! የዩስ ኮንግሬስ እጩ ተወዳዳሪ ሳም ሌካርዶን ለአሜሪካ ኮንግሬስ አባል እንዲሆኑ ድምጾን ይስጡ!!!

SUPPORT SAM TODAY

VOLUNTEER TODAY